ለ2013 ዓ.ም የት/ዘመን በመደበኛው እና በተከታታይ መረሃ-ግብር ለድህረ-ምረቃ ፕሮግራም ትምህርት አመልካቾች
የጎንደር ዩኒቨርስቲ ለ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በድህረ ምረቃ ፕሮግራም በመደበኛው (በቀን) መርሃ ግብር ለሁለተኛ እና ለሶስተኛ ዲግሪ እንዲሁም በተከታታይ (ቅዳሜና እሁድ) መርሃ ግብር ለሁለተኛ ዲግሪ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ስለሆነም የትምህርት አሰጣጡ የኮረና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ወረርሽኝ እስከሚሻሻል ድረስ በቨርቹዋል የመማር-ማስተማር መንገድ በተጨማሪም እንደ አስፈላጊነቱ በገጽ ለገጽ የሚካሄድ መሆኑን እያሳወቀ ፍላጎት ያላቸውን ብቁ አመልካቾች የሚከተሉትን መሰፈርቶች በማሟላት በኦንላየን ማመልከት እንደምትችሉ እንገልፃለን፡፡
- የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲው ድረ-ገጽ (https://portal.uog.edu.et) መሙላት፤
- በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻል ፈንድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000018782492 የማመልከቻ ለሁለተኛ ድግሪ 100.00 ብር (መቶ ብር)/ሶስተኛ ድግሪ 200.00 ብር/ መክፈልና ከባንክ ያገኙትን Tr.Ref. ቁጥር በማሰገባት ኦንላየን የማመልከቻ ቅፁን ማጠናቀቅ፤
- ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመልከቻ ፎርሙ በመመለስ ፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን፣ የወጪ መጋራት ሰነድዎትን፣ ባንክ የከፈሉበትን ደረሰኝ እንዲሁም የትምህርት ወጪዎን /Sponsorship/ የሚሸፍንልዎት የመንግስት መስሪያ ቤት ከሆነ የተፈረመበትና ማህተም የተደረገበት ፎርም አስገብተው እና ሌሎች መረጃዎችን በማከል ምዝገባዎትን ማጠናቀቅ ይኖርብዎታል፡፡
- የእስፖንሰርሺፕ/Sponsorship/ ቅፅ ከዩኒቨርስቲው ድረ ገጽ http://uog.edu.et/registrar/forms/ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ለPhD አመልካቾች የ BA/BSc ዲግሪ/ጊዜያዊ ዲግሪ እና CGPA ያለው ትራንስክሪፕት እና የMA/MSC ዲግሪና ትራንስክሪፕት ማያያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
- በተጨማሪም ለPhD አመልካቾች ትምህርት ክፍሉ የሚጠይቀውን መስፈረት ማያያዝ ይኖርብዎታል፡፡
- ለሁለተኛ ድግሪ/M.Sc/M.A/ አመልካቾች የመጀመሪያ /BSc/BA ዋናውን/ጊዜያዊ ዲግሪ እና CGPA ያለው ትራንስክሪፕት ማያያዝ ይጠበቅባችኋል፡
- የትምህርት ማስረጃና ሌሎች ሰነዶችን ዋናውን/ኦሪጅናሉን በተጠየቃችሁ ጊዜ ሁሉንም የማቅረብ ግዴታ አለባችሁ፡፡
- ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ለጎንደር ዩኒቨርስቲ ዋናው ሬጅስትራር ቢሮ ፖስታ ሳጥን ቁጥር 196 ቀደም ከተማራችሁበት ተቋም በወቅቱ ማስላክ አለባችሁ፡፡ ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ያላስላከ አመልካች በቀጣይ የምዝገባ ሂደቶች የማይሰተናገድ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ
- ምዝገባው የሚከናወነው በተጠቀሰው የማመልከቻ ጊዜ ማለትም ከመስክረም 04, 2013 ዓ.ም እስከ መስከረም 17, 2013 ዓ.ም በኦንላየን ብቻ ሲሆን ምንም አይነት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ማስገባት አይቻልም፡፡
- የፈተና ግዜውን በተመለከተ ከትምህርት ክፍሉ ማስታወቂያ ሰሌዳ እንዲሁም ከዩኒቨርስቲው ድረ ገፅ (http://uog.edu.et/registrar/category/announcement) መከታተል የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- በምዝገባ ወቅት የምታገኙትን አፕሊኬሺን ቁጥር ወይም ለምዝገባ የተጠቀማችሁበትን ስልክ ቁጥር በማሰገባት የማመልከቻ ሂደቱን መከታተል ትችላላችሁ፡፡
- የአመልካቾች ቁጥር ከት/ክፍል የመቀበል አቅም (ከዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሌጅስትሌሺን) በታች ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የመመዝገቢያ ቀን፡ ከመስከረም 05, 2013 ዓ.ም እስከ መስከረም 17, 2013 ዓ.ም
የጎንደር ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት
